Sunday, May 22, 2011


በዚህ ቦታ ላይ የእግዚአብሔር ልጆች /መላእክት/ ተብለው የተጠሩት ረቂቃኑ መላእክት ሳይሆኑ ሥጋ ለባሽ የሆኑ ደቂቀ ሴት (በአቤል ፈንታ አዳም የወለደው የሴት ልጆች) ሲሆኑ (ዘፍ. 4$25) የሰው ልጆች የተባሉት ደግሞ የቃየል ልጆች ናቸው፡፡ ይኽንንም ምስጢር ‹‹አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገ ሄኖክ›› እንዲህ ሲል ገልጾታል፡፡ #የሰው ልጆች ከበዙ በኋላ እንዲህ ሆነ፡፡ በዚያ ወራትም መልከ መልካሞች ደመግቡዎች ልጆች ተወለዱላቸው፡፡ በደብር ቅዱስ ያሉ ደቂቀ ሴትም እነሱን አይተው ወደዱአቸው፡፡ እርስ በርሳቸውም ኑ ለኛ ከቃየል ልጆች ሴቶችን እንምረጥ ለኛ ልጆችን እንውሰድ አሉ$ (መጽ.ሄኖክ 1$1-3)፡፡
ደቂቀ ሴት ስለምን የእግዚአብሔር ልጆች /መላእክት/ ተባሉ?
1. ስለአለቅነታቸው፡-
የግእዙ መጽሐፍ ቅዱስ መላእክት በማለት ይጠራቸዋል፡፡ መልአክ የሚለው ቃል የግእዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም አለቃ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ ‹መልአክ› የሚለውን ቃል ‹‹አለቃ›› ማለት መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡ ለምሳሌ በዮሐንስ ራእይ 21፣8-12 ላይ ያለውን ቃል ብንመለከት ጥሩ አስረጅ ይሆናል፡፡ በእነዚህ ሥፍራዎች #ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ$ ተብሎ እናገኛለን፡፡ ይህ መልእክት ደግሞ ለሰማያውያን መላእክት ለነ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል የተላከ እንዳልሆነ የታወቀ ነው፡፡ ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት አለቆች የተላከ እንጂ፡፡ ዛሬ ‹እገሌ የዚህ ደብር አለቃ ነው› ተብሎ እንደሚጠራው ሁሉ #በኤፌሶን ላለች ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ (አለቃ)›› ለሚልከው መልእክት ‹‹በኤፌሶን ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ$ ተብሏል፡፡ ደቂቀ ሴትም /የሴቶች ልጆችም/ መላእክት መባላቸው አለቆች በመሆናቸው ነው፡፡
 2. ስለ ን ጽሕናቸውና ቅድስናቸው፡-
ከሴት ልጆች መካከል በደብር ቅዱስ ከሴት ርቀው፣ ንጽሕ ጠብቀው፣ በጾም ተጠምደው፣ የሚኖሩ ስለነበሩ በዚህ ግብራቸው መላእክትን መስለዋልና የእግዚአብሔር ልጆች በመባል ተጠርተዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደ እግዚአብሔር ትዕዛዝ የሚኖሩትን ሰዎች የእግዚአብሔር ልጆች ይላቸዋል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በቀዳማዊ ክታቡ #የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደሰጠን እዩ$ ብሏል (1ዮሐ. 3$1)፡፡ በጥምቀት የእግዚአብሔር ልጆች እንደምንሆን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምል፡፡ #ዳግመኛ ልትወለዱ ያሰፈልጋችኋል$ ሲል፡፡ ይህም ደግሞ በጥምቀት የሚገኝ ጸጋ ነው (ዮሐ. 3$1)፡፡
 
ከላይ በተገለጸው ምክንያት ደቂቀ ሴትን የእግዚአብሔር ልጅ ብሎ በመጥራት በኃጢአታቸው ከእግዚአብሔር መንገድ ከወጡት ከቃየል ልጆች ጋር በፈጸሙት ዝሙት እግዚአብሔር እንዳዘነባቸው ቅዱስ መጽሐፍ አስረድቷል፡፡ ዳሩ ግን የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት ሰማያውያን መላእክት ናቸው የሚለው አመለካከት ስሕተት መሆኑን የምንረዳው ከቅዱስ መጽሐፍ ባገኘነው ትምህርት መሠረት ነው፡፡ ቀደም ተብሎ እንደተጠቀሰው የእግዚአብሔር ቃል ሰማያውያን መላእክት በተፈጥቸው /በባሕርያቸው / ማግባት፣ መጋባት፣ መብላት፣ መጠጣት የለባቸውም፡፡ ፍትወተ ሥጋ የሥጋ ለባሹ የሰው ልጅ ተፈጥዊ ባሕርይ ነው፡፡ ስለዚሀ ሰማያውያን መላእክት ከሰው ልጆች ጋር በፍትወት አልወደቁም (ማቴ.22$30)፡፡

የመላእክት መላእክት በአፈጣጠራቸው ረቂቃን መናፍስት በመሆናቸው እንደ ሥጋ ለባሽ ፍጥረታት አይበሉም፣ አይጠጡም፣ አያገቡም (ማቴ 22$30፡፡ ሉቃ 24$39)፡፡ ጾታም የላቸውም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ግን መላእክት በአንድ ወቅት ከሰው ልጆች ጋር እንደወደቁ አድርገው ይናገራሉ፡፡ ለዚህም መረጃ አድርገው ለማቅረብ የሚሞክሩት ‹‹የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች አገቡ›› የሚለውን ኃይለ ቃል ነው (ዘፍ.6$2)፡፡

No comments:

Post a Comment