Monday, November 12, 2012

  ካህኑ ለምን በእጁ ያሳልመናል?የካህኑን   እጅ መሳለም፦ አንዳንድ ሰዎች ካህኑ ለምን በእጁ ያሳልመናል ይላሉ።ነገርግን ሚስጢሩ ይሄ ነው የካህኑ እጅ እኮ እሳታዊያን የሆኑ መላዕክት መንካት የማይቻላቸውን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የዳሰሰበት ነው። በቅዳሴ ላይ ቅዱስ ሥጋውን መንካት የሚችለው ዋናው ካህን ብቻ ነው ፤ ሁለተኛው ካህን እንኳን መንካት አይችልም። ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የዳሰሰበት ስለሆነም ካህኑ በእጁ ያሳልመናል እኛም የተቀደሰውን የጌታ ስጋና ደም የተዳሰሰበት እጅ እየተሳለም የቅዳሴው በረከትና የአምላካችን ምህረት በእኛ ላይ እንዲሆን አሜን አሜን እንላለን።ድንቅ መለኮታዊ ሚስጢር ማለት
እንዲህ ነው..አንሥኡ እደዊክሙ ቀሳውስ ፦ ዲያቆኑ ይህን በሚልበት ጊዜ ንፍቁ ካህን ማሕፈዱን ከጻሕሉ ላይ ያነሳል ፤ ይህም የጌታ መልአክ የመቃብሩን ድንጋይ የማንከባለሉ ምሳሌ ነው። ከዚህ በኋላ ጌታችን በምሴተ ሐሙስ ሕብስቱን እንደያዘው ዋናው ካህንም ሕብስቱን ከፍ አድርጎ ይይዘዋል ፤ ይህም የጌታ ትንሣኤ ምሳሌ ነው።


    እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ፦ በእግዚኦታ ላይ ካህኑ ሕብሥቱን ይበልጥ ከፍ አድርጎ ይይዘዋል ይህም የዕርገቱ ምሳሌ ነው። ከካህኑ ጋር ሆነን 41 ግዜ እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ እንላለን ፤ ይህም አርባው እግዚኦታ አይሁድ ጌታችንን 40 ግዜ እንገርፋለን ብለው እያዛቡ ብዙ ግዜ የመግረፋቸው ምሳሌ ሲሆን በመጨረሻ ካህኑ ብቻውን የሚላት እግዚኦታ ደግሞ የአዳምና የሔዋን የንስሃ ምሳሌ ነው። 12 ግዜ እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ ስንል ደግሞ ስለስምህ ብለህ ይቅር በለን ስንል ነው።“አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ” የሚለውን እያንዳንዱን ፊደል ስንቆጥር 12 ይሆናልና!!እንዲሁም 12ግዜ በእንተእግዚትነ ማርያም መሐርነ ክርስቶስ ስነንል ደግሞ ስለእናትህ ብለን ማረን ማለታችን ሲሆን*ቅድስት ድንግል ማርያም*የሚለውን እያንዳንዱን ፊደል ስንቆጥር 12 ይሆናልና ነው

በእግዚኦት ላይ የሚሰማው ቃጭል፦ በእግዚኦት ላይ የሚሰማው ቃጭል የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በቀራንዮ ልጇን ፊት ለፊት በመስቀል ላይ እያየችው ያዘነችው ኃዘን ያለቀሰችው ልቅሶ ምሳሌ ነው። አረጋዊው ስምኦን ወላኪሰ ይበውእ ውስጠ ልብኪ /በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል እንዳላት/ ሉቃስ 2:35 ይህ ሃዘን ከባድ ነውና ፤ መላእክት ባያጽናኗት ኖሮ ሃዘኑ ለሞት ባበቃት ነበር ይላል!! ታላቅ ሃዘን ነበርና; በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል የተባለውም ይህ ከባድ ሃዘን ነው።


No comments:

Post a Comment