Sunday, May 22, 2011

ምንጭ :- ማህበረ ቅዱሳን

. መፍረድ አይገባም«እንዳይፈረድብህ አትፍረድ» ይላል ጌታ፡፡ /ማቴ 7፥1/ ለመፍረድ ማንም ስልጣን አልሰጠንም፡፡ ኧረ ለመሆኑ አባቶች የተሸከሙትን ፈተና ሞክረን አይተነዋል ወይ? እኛ ብንሆን እንደነርሱ እንደማንሆን ምን ማረጋገጫ አለን? አባቶቻችን ዓለምንና ክብርን ንቀው፣ ራሳቸውን ለምንኩስናና ራስን የመካድ ኑሮ አሳልፈው ሰጡ፡፡ ከእነርሱ መካከል የተውትን ክብር የናፈቁ፣ የካዱት እኔነታቸው እያሸነፋቸው ይኖራሉ፡፡

በእነዚህ አባቶች ላይ እጆቻችን የምንቀስር ስንቶቻችን ይህንን ክብርንና ራስን የመካድ ኑሮ ሞክረነው እናውቃለን፡፡ አብዛኞቻችን የምዕራባውያንን የተንደላቀቀ ኑሮ የለመድን፣ የምንኩስናንና የተጋድሎን ኑሮ እንኳን የምንሞክረው ቀርቶ ስንሰማው የሚያንገሸግሸን፣ አንዳንዴም የምንቀላለድበት አይደለምን? ታዲያ እንዴት ሞክረውት የተሸነፉትን ለመውቀስና ለመኮነን እንፈጥናለን?

ምናልባት «ብንማርና አባቶች የሚገባውን ሁሉ ቢያደርጉልን እንደተባለው እንሆን ነበር» እንል ይሆናል፡፡ አይሁድም «በአባቶቻችን ዘመንስ በነበርን ኑሮ ነቢያትን ባልገደልን ነበር» ሲሉ ጌታ ገሠጻቸው እንጅ በዚያ አላመሰገናቸውም፡፡ /ማቴ 23፥30/ ይህንን ፍርድ ለእግዚአብሔር ትተን ለራሳችን መዳን ብንሠራ ግን መልካም ይሆናል፤ ፍርዱን ግን ለእርሱ እንተወው «በቀል የእኔ ነው» ብሏልና፡፡ / /

ይህ ማለት ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ሲታወኩ ዝም ትላለች ማለት አይደለም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ለምዕመናን መገልገል እንቅፋት የሚሆኑና የሚፈጥሩ አባቶች ከቤተ ክርስቲያን የሚለዩበት ሥርዓት አለ፡፡ ምዕመናን በአገልግሎት ተዋረድ አማካኝነት ችግራቸውንና አቤቱታቸውን ለሚመለከተው አካል ማድረሳቸውም ችግር አይደለም፡፡ ችግሩ በየመንገዱና በየቀልዱ አባቶችን በመስደብና በእነርሱ ላይ ለማላገጥ የውሸት «መንፈሳዊነታችን» ለመግለጥ ስንጥር ነው፡፡ ከእውነት ለቤተ ክርስቲያን የሚቆረቆር ሰው የአባቶችን ውድቀት እየከፋውና ልቡ እያዘነበት በግድ ያወራዋል እንጅ፤ የካም ልጅ በኖህ ስካር እንደሳቀው በአባቶቹ «ስካር» አይዝናናም፤ አይቀልድም፡፡

No comments:

Post a Comment